የቤተሰብ ተሳትፎ አማካሪ ቡድን (FEAT)ማመልከቻ
2020-2021
Sign in to Google to save your progress. Learn more
MCPS Logo
ምንም ዓይነት የገቢ ወይም የበፊት ታሪክ ቢኖር- ወላጆች/ሞግዚቶች በልጆቻቸው ትምህርት ላይ ትኩረት ሰጥተው በሚጥሩበት ጊዜ የተማሪ ትምህርት ላይ መገኘት/መከታተል፣ ውጤት፣ ማኅበራዊ ግንኙነት፣ ባሕርይ፣ የመመረቅ ብዛት መጠን እየተሻሻለ እንደሚሄድ ከ40 ዓመታት በላይ የተጠኑ ማስረጃዎች ያሳያሉ። የሞንትጐመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ፣ ስለ ትምህርት ፕሮግራሞችና ተነሳሽነት ግንዛቤ ኖሯቸው ግብረመልስ/ግብዓት ለመስጠት እንዲችሉ አዳዲስ እድሎችን በመስጠት ቤተሰቦች የለውጥ ሞዴል እንዲሆኑ ይፈልጋሉ።  

ራዕይ
ቤተሰብን በውሳኔ አሰጣጥ እና በፕሮግራም ግምገማ/ክለሳ ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ የተማሪዎችን የትምህርት ቤት ተሞክሮ እና አካዴሚያዊ ስኬት እንዲሻሻል እና ፍትሃዊ የትምህርት ዕድሎች መኖራቸዉን ማረጋገጥ። በተለይ ቡድኑ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ወላጆችና ሞግዚቶች ግብአት እና ግብረመልስ እንዲሰጡ እንዲያግባቡ ይፈቅዳል፤ ብሔራዊ PTA ስለመተግበር “Four Is” framework for Transformative Family Engagement የቤተሰብ ግንኙነቶች እርስ በርሱ የሚጣጣም፣ በግል የሚሰራ፣ የተቀናጀና ውጤታማ መሆንን ያረጋግጣል፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤቶች እና ዲስትሪክት አቀፍ የሚሰጥ ውሳኔ ወጥነት ያለው እና የተሻለ አሰራርን ይፈጥራል።

ተልዕኮ/ዓላማ
ጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ የቤተሰብ-ትምህርት ቤት አጋርነት ደረጃዎችን ለማዳበር በትምህርት ቦርድ ፖሊሲ ABC የወላጅ እና የቤተሰብ ተሳትፎ፣ 1) ሁሉንም ቤተሰቦች ወደ ትምህርት ቤት ማህበረሰብ ጥሩ አቀባበል ማድረግ፣ 2) ውጤታማ የሆነ ግንኙነት ማድረግ፣ 3) የተማሪዎችን ስኬት መደገፍ፣ 4) ስለእያንዳንዱ ልጅ ማቀንቀን፣ 5) ኃላፊነት ማጋራት፣ እና 6) ከማህበረሰብ ጋር በትብብር መስራት።  
ኃላፊነቶች
>     ከቤተሰቦች እና የወላጅ አካዴሚ ጋር ግንኙነትን ጨምሮ፣ ስለ ፕሮግራሞች፣እንቅስቃሴዎች ፣የአገልግሎት ሪሶርሶች፣ እና ቁሳቁሶች ለ MCPS ማዕከላዊ ቢሮ ሠራተኞች፣ ለት/ቤት ሰራተኞች እና ለስራ ቡድኖች ግባት እና አስተያየት ማቅረብ።
> በማህበረሰቡ ውስጥ ካሉ ሌሎች ወላጆች ግብረመልስ መጠየቅ/መፈለግ።
> በሁሉም ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚጋብዝ/የሚስብ ኣካባቢ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ላይ መሳተፍ።
> የቤተሰብን የማቀንቀን/ጥብቅና መቆም ችሎታዎች ለማጠንከር ሠራተኛን በስልጠና መርዳት።
> ከሁሉም ተማሪ እና ቤተሰብ ጋር በፍትኃዊነትና በእኩልነት በጋራ የመማር ዕድል እንዲዳብር/እንዲጨምር ለማድረግ ለትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች እና ለመምህራን የትብብር እቅድ ማዘጋጀት።

መዋቅር
የቤተሰብ ተሳትፎ አማካሪ ቡድን (FEAT) ግለሰቦችንና ባለድርሻ አካላትን፣ የትምህርት ቤት አስተዳዳሪን፣ አስተማሪን፣ የወላጅ-ማህበረሰብ አስተባባሪን እና የተማሪዎች እና የቤተሰብ ድጋፍና ተሳትፎ አስተባባሪን ጨምሮ ቁጥራቸው ከ25 ያልበለጠ ወላጆች/ሞግዚቶችን ያቀፈ ቡድን ነው። ማስታወሻ፦“ወላጅ” የሚለው ቃል በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተመዘገበ/ች ልጅ ወላጅ ወይም ህጋዊ አሳዳጊ/ሞግዚትን ያመለክታል።

ማመልከቻ
የተሞላው ማመልከቻ ሜይ 21/2021። ለበለጠ መረጃ ለተማሪ ፣ ለቤተሰብ እና ለትምህርት ቤት አገልግሎቶች በ 240-740-4620 ይደውሉ ፡፡  

ምርጫ
ሰፋ ያለ ውክልና ለማረጋገጥ፥ ማመልከቻዎች የመኖሪያ ቦታን፣ የልጁ/ልጅቷ የትምህርት ደረጃን፣ እና ከ MCPS ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ጋር የተዛመዱ ፍላጎቶች እና ልምዶች በእነዚህ ብቻ ሳይወሰኑ ሥርዓተ ትምህርት፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች፣ ልዩ ትምህርት፣ ተሰጥኦ እና ችሎታ፣ እና እንግሊዝኛ ለሌሎች ቋንቋ ተናጋሪዎች (ESOL) ን ጨምሮ፣ ብዙ ጉዳዮችን ግምት ዉስጥ በማስገባት ይገመገማሉ። የቤተሰብ ተሳትፎ አማካሪ ቡድን አባልነት የተማሪን ህብረተሰብ የዘር እና የብሄር ብዙህነት/ስብጥር ያንፀባርቃል። እንዲያገለግሉ የተመረጡት አባላት ጁን 4/2021 እንዲያውቁ ይደረጋል።

ስብሰባዎች
የቤተሰብ ተሳትፎ አማካሪ ቡድን በአንድ ሙሉ የትምህርት ዓመት ቢያንስ ሰባት ጊዜ ይሰበሰባል። እንደአስፈላጊነቱ የትርጉም አገልግሎቶች ይሰጣሉ። ከወቅቱ አባላት ጋር በመተባበር የስብሰባ ቀኖች እና ጊዜዎች መርኃግብር ይዘጋጃል።

ከአባላት የሚጠበቁ
እያንዳንዱ አባል ለሁለት ዓመት ያገለግላል። የቡድኑን ሥራ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የጊዜ ገደብ በምርጫ ቀን ላይ በመመርኮዝ ይስተካከላል። አባላት መርሐግብር በተያዘላቸው ስብሰባዎች ላይ የመገኘት፤ አስቀድሞ የቀረበላቸዉን የስብሰባ ቁሳቁሶች መገምገም/መከለስ፤ እርስበራሳቸዉ እና ከት/ቤት ስርዓት ሰራተኞች ጋር በትብብር መሥራት፤ አመለካከቶችን እና አስተያየቶችን በግልጽ፣ ገንቢ በሆነ መልኩ፣ እና በአክብሮት መግለፅ፤ እና በማህበረሰባቸው ውስጥ የቤተሰብን ተሳትፎ ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል። አባላት ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ ስሞቻቸው እና የኢሜይል አድራሻቸው በይፋ ለህብረተሰብ ይገለጻል።

ከ MCPS የሚጠበቅ
የተማሪ እና የቤተሰብ ድጋፍ እና ተሳትፎ (SFS) ሠራተኞች ከተባባሪ ሊቀመንበር ጋር በጋራ በመሆን አጀንዳዎችን በማዘጋጀት ከእያንዳንዱ የስብሰባ ጊዜ አስቀድሞ (እንደአስፈላጊነቱ በተለያዩ ቋንቋዎች) ለስብሰባዎቹ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ለአባላት ይልካሉ። ለ MCPS ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች እና ሠራተኞች የቡድኑ ሥራ ወቅታዊ መረጃዎች እንዲገኙ ይደረጋል። የ MCPS ሠራተኞች ማንኛውም የቡድኑ ምክረ ሐሳብ የሚገኝበትን ሁኔታ በተመለከተ በ60 ቀናት ውስጥ ለቤተሰብ ተሳትፎ አማካሪ ቡድን ሪፖርት ያደርጋሉ።

የአመልካች መረጃ/ኢንፎርሜሽን
ስም *
የመላኪያ አድራሻ *
እባክዎን የጎዳናውን ቁጥር ፣ ሙሉ የጎዳና ስም ፣ ከተማ ፣ ግዛት እና ዚፕ ኮድ ያክሉ
የቤት ስልክ *
የስራ ስልክ *
ሞባይል ስልክ *
ኢ-ሜይል *
አመልካች ቀጥሎ በተመለከተዉ ትምህርት ቤት(ቶች) የሚማር/የምትማር ልጅ(ጆች) ወላጅ ነው/ናት፦ *
ይህኛውን መረጃ የመግለጽ ግዴታ የለብዎትም (የሁሉንም ቤተሰቦች እና ተማሪዎች ውክልና ለማረጋገጥ የተጠየቀ)
ዘር፦
ጾታ፦
እቤት ዉስጥ የሚነገሩ ቋንቋዎች፦
ግንዛቤ ውስጥ የሚያሻቸው ነገሮች፦
ለማህበረሰብ ባለድርሻ አካላት
ድርጅት
ማእረግ/የስራ ድርሻ
ሁሉም አመልካቾች
የ MCPS የቤተሰብ ተሳትፎ አማካሪ ቡድን ጠቃሚ/ተፈላጊ አባል መሆን እችላለሁ ብለዉ የሚያምኑበትን ምክንያት ያብራሩ። ከ MCPS ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ጋር የተዛመዱ ፍላጎቶች እና ልምዶች በእነዚህ ብቻ ሳይወሰኑ ሥርዓተ ትምህርት፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች፣በህብረተሰብ ዉስጥ ተሳትፎ፣ ልዩ ትምህርት፣ ተሰጥኦ እና ችሎታ፣ እና እንግሊዝኛ ለሌሎች ቋንቋ ተናጋሪዎች (ESOL) ን ጨምሮ መረጃዎችን ያካቱ። *
ስለ MCPS እና የወላጅ አቀንቃኝነት ምን ለመማር እንደሚፈልጉ ያብራሩ? *
Submit
Clear form
Never submit passwords through Google Forms.
This form was created inside of Montgomery County Public Schools. Report Abuse