የትንቢተ ሐጌ ዓላማ፣ አስተዋጽኦ እና ዐበይት ትምሕርቶች
ጥያቄዎቹን ከመስራትዎ በፊት ለጥናት አመቺ ጊዜ መድበው በጸሎት የጥናቱን ክፍል እና ከላይ የቀረበውን ማብራሪያ በጥንቃቄ እንዲያነቡ እንመክራለን፡፡ ጥናቱን የሚያደርጉት  በቡድን ከሆነ (Bible study group)፣ በማብራሪያው ውስጥ ያሉትን የውይይት ጥያቄዎች በመጠቀም ጥናቱን ይበልጥ ፍሪያማ ማድረግ ይቻላል፡፡ በጥያቄዎቹ ላይ አስተያየት ወይም ማሻሻያ ቢኖርዎ በሚከተለው የኢ-ሜይል አድራሻ ይጻፉልን፡፡ tsegaewnet@gmail.com መልካም የጥናት ጊዜ፡፡
Sign in to Google to save your progress. Learn more
Email *
1 እግዚአብሔር ሐጌን የጠራበት ዓላማ፣ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ የተመለሱት አይሁድ ከ70 ዓመታት በፊት የተደመሰሰውን ቤተ መቅደስ በመሥራት ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር እንዲገልጡ ማበረታታት ነበር። *
1 point
2 ትንቢተ ሐጌ፣ መሪዎች የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ ማድረግ ስላለባቸው ነገሮች የሚያስተምር መርሆች የሚገኝበት መጽሐፍ ነው። *
1 point
3 ትንቢተ ሐጌ የሚያስተምረው፥ በሕይወት ውስጥ እውነተኛ በረከትን ለማግኘት፥ ማለትም ሥጋዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ በረከት ጨምሮ እንዲኖር፥ እግዚአብሔር እንድንሠራው የሚፈልገውን ነገር በተቀዳሚ የመሥራት ፍላጎት መኖር እንዳለበት ነው። *
1 point
4 ለክርስቲያኖች፥ እግዚአብሔርን ከታዘዝን ሥጋዊ በረከቶችን እንደምናገኝ የተገባልን ቃል ኪዳን የለም፡፡ *
1 point
5 እግዚአብሔር ለአይሁዶች ያለው አሳብ የቤተ መቅደሱ ሕንጻ ሥራ መጠናቀቅ በራሱ እንደ ተልዕኳቸው ማብቂያ እንዲታይ ነበር፡፡ *
1 point
6 ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ አይሁድ ከእግዚአብሔር ይልቅ ቤተ መቅደሱን ያከብሩ ነበር። *
1 point
7 “በእውነትና በመንፈስ” እስከሆነ ድረስ ሰው የትም ቦታ እግዚአብሔርን ሊያመልከው ይችላል፡፡ *
1 point
8 የቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ብዙ ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር እንጂ የተለየ አትኩሮት ወይም ቅድስና የለውም። *
1 point
9 የመጀመሪያው የሐጌ መልእክት የተሰጠው በነሐሴ ወር _____ ዓ.ዓ. ነበር። *
1 point
10 የመጀመሪያው የሐጌ መልዕክት ዓላማ ቤተ መቅደሱ ፈርሶ ሳለ ሕዝቡ በራሳቸው ጉዳይ እንዴት እንደተጠመዱ ለማሳየት ነበር። *
1 point
11 ሐጌ የመጀመሪያውን መልእክት ካቀረበ ከስንት ቀናት በኋላ ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን መሥራት ጀመሩ ? *
1 point
12 _____________ ዓላማ እግዚአብሔር የእርሱን ነገር ባለማስቀደማቸው ነሥቶአቸው የነበረውን በረከት እንደገና እንደሚመልስላቸው በመናገር ሕዝቡን ማበረታታት ነበር። *
1 point
13 _____________ዓላማ እግዚአብሔር ዘሩባቤልን “የቀለበት ማኅተም" አድርጎ እንደመረጠው ለሕዝቡ መግለጽ ነበር። *
1 point
14 ኢየሱስ የዘሩባቤል ዘር ስለሆነ ትንቢተ ሐጌ የሚደመደመው ስለሚመጣው መሢሕ በመናገር ነው። *
1 point
A copy of your responses will be emailed to the address you provided.
Submit
Clear form
reCAPTCHA
This content is neither created nor endorsed by Google. Report Abuse - Terms of Service - Privacy Policy