በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ለመመረቂያ ጽሑፍ የተዘጋጀ ቃለ መጠይቅ
ውድ የመጠይቁ ተሳታፊ፡ የዚህ መጠይቅ ዋና አላማ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ስለንስሃ አባት ያላቸውን እውቀትና አመለካከት ለማወቅና የመፍትሄ ሀሳቦችን ለማቅረብ የተዘጋጀ ሲሆን እርስዎ የሚሰጡት መልስ ለጥናቱ መሳካት ትልቅ ድርሻ እንዳለው በመረዳት እንዲሞሉ በአክብሮት እየጠየኩ የሚሰጡት መልስ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቂ መሆኑን እገልፃለሁ፡፡ በመጠይቁ ላይ ስም መፃፍ አያስፈልግም፡፡ መመሪያ፡ ጥያቄዎችን በጥሞና ካነበቡ በኃላ ምርጫ ለሚጠይቁ መልሶች በተሰጠው ሳጥን ውስጥ የ"√" ምልክት ያስቀምጡ ነገር ግን ማብራሪያ ለሚጠይቁት ጥያቄዎች በክፍት ቦታው ላይ መልስዎን ይፃፉ፡፡ መጠይቁን ለመሙላት ስለተባበሩኝ እግዚአብሔር ያክብርልኝ!