Shoreline School District 2022-23 Budget Feedback Form
የዚህ ቅጽ አላማ የዲስትሪክትና ማህበረሰብ ባለድርሻ አካላት በ2022-23 የበጀት እቅድ ስራ ላይ ግብረመልስ እንዲሰጡ እድል መስጠት ነው። የትምህርት ቤቱ ዲስትሪክት እስከ ነሀሴ 31፣ 2022 ድረስ ለሕዝብ ትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ጽሕፈት ቤት ሚዛናዊ የሆነ በጀት ማቅርብ ይጠበቅበታል።

እንደ ዲስትሪክትና ማህበረሰብ፣ በሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉትን ኢ-ፍትሃዊነቶችን ለመቅረፍ የ BIPOC ተማሪዎቻችንን እና ከትምህርታዊ ፍትህ በጣም የራቁትን የእድል ክፍተቶችን ለመቅረፍ ለሥራችን ዋና እሴቶችን እና አላማዎችን እንገዛለን።

የበለጠ በተሟላ መልኩ ለመደገፍ እና ለመማር እና ለደህንነት የላቀ ብቃት ለሁሉም ተማሪዎች ለማቅረብ ያለንን ቁርጠኝነት ከፍ ለማድረግ፣ የዘር እና ፍትሃዊነት ውሳኔ ሰጭ መሳሪያ ተዘጋጅቷል፤ ይህም የውሳኔ አሰጣጡ ሂደት አንጸባራቂ፣ አሳቢ እና ከእኛ ራእይ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ነው። መሳሪያው የሚከተሉትን ጥያቄዎች ያካትታል፦ 1) ለአፍታ ቆም ብለው ራስዎን ይመርምሩ - ማን ነዎት? (እንደ ግለሰብ እና ውሳኔ ሰጪ ቡድን) 2) ማን ነው ተጽእኖ የሚያደርስበት? 3) ተጽእኖዎቹ ምንድን ናቸው? 4) ምን የተፈጠረ ይመስልዎታል?

የመሳሪያው አላማ በShoreline ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚሳተፉትን ሁሉ፡ ዘር እና ፍትሃዊነት በትምህርት፣ በፕሮግራም ንድፍ፣ በሰራተኞች፣ በገንዘብና ፖሊሲ ምርጫዎች ላይ እንዴት ተጽእኖ እንደሚያሳድሩ እንዲማሩ፣ እንዲያስቡና እንዲፈቱ ማድረግ ነው። ሁሉም የShoreline ትምህርት ቤቶች ማህበረሰብ አባላት በሁሉም እንቅስቃሴዎቻችን እና ምርጫዎቻችን ላይ ጸረ-ዘረኝነት ልማዶችን እና የፍትሃዊነት ግንዛቤን ለማሻሻል መጣር አለባቸው።

ውጤቶቹ አሁንም ተመራጭ የማይሆኑባቸው ጊዜያት እንደሚኖሩ እንገነዘባለን እና የበለጠ ፍትሃዊ ውጤትን የማግኘት እድልን ለሚጨምር ፍትሃዊ ሂደት እውነተኛ የመሆን አላማ አለን። ስለ ወቅታዊው ሁኔታና ስለ ወደፊት እቅድ ለምናደርገው ተጨማሪ ትንታኔ (ከ2022-23 በላይ) ተጽእኖዎችን በተመለከተ የሚከተሉት ጥያቄዎች ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው፦ ውሳኔው ፍትሃዊነትን ሊያሳድግ የሚችለው በምን መንገዶች ነው? ይህንን ፍትሃዊ ውሳኔ ለማድረግ የሚያስችሉምን ምን ግብዓቶች አሉ? ሊሆኑ የሚችሉ ተግዳሮቶች፣ መዋቅራዊ መሰናክሎች ወይም ያልተጠበቁ ነገሮች ምንድን ናቸው?
እንደ የምዝገባ መቀንስ እና የግዛት የገንዘብ ድጋፍ ውሱንነት አስቸጋሪ የውሳኔ መነሻዎች የሚያቀርቡልንን ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ለአሁኑ የበጀት እቅድ ሂደት እነዚህ ጥያቄዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው።

አሁን ያለው የዕቅድ ሂደት በጊዜ እና ባሉት ግብዓቶች የተገደበ መሆኑን ብናውቅም፣ በዚህ አጭር ዳሰሳ ጥናት ከእርስዎ የምንሰበስበው መረጃ ከመጪው የትምህርት ዘመን ባለፈ የዲስትሪክቱን የወደፊት የበጀት እቅድ ለማሳወቅ ይጠቅማል። ከባለድርሻ አካላት ጋር አሁን እና ወደፊት በመተባበር፣የ ኣShoreline ትምህርት ቤት ዲስትሪክት ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ቤተሰቦች ላይ ተጽእኖ የሚያደርሱ ውሳኔዎች ላይ ይህ መሳሪያ እንዲተገበር ማበረታታታችንን እንቀጥላለን።

በዚህ ስራ ላይ ስላበረከቱት አስተዋጽኦ እና በዚህ ሂደት ውስጥ እኛን ለማገዝ ስለስጡን ጊዜ እና ችሎታዎ እናመሰግናለን።
Sign in to Google to save your progress. Learn more
1. ስም (አማራጭ)
2. ስነ-ሕዝብ (ዘር) - አንድ ኦቫል ላይ ብቻ ምልክት ያድርጉ።
Clear selection
3. እኔ ... - የሚመልከታቸውን ሁሉ ይምረጡ።
እባክዎ ጥያቄዎን ወይም ግብረመልስዎን ከዚህ በታች ያጋሩ፦ *
Submit
Clear form
Never submit passwords through Google Forms.
This form was created inside of Shoreline School District. Report Abuse