የትንቢተ ዕንባቆም ዓላማ እና ዋና ዋና ትምሕርቶች
ጥያቄዎቹን ከመስራትዎ በፊት ለጥናት አመቺ ጊዜ መድበው በጸሎት የጥናቱን ክፍል እና ከላይ የቀረበውን ማብራሪያ በጥንቃቄ እንዲያነቡ እንመክራለን፡፡ ጥናቱን የሚያደርጉት  በቡድን ከሆነ (Bible study group)፣ በማብራሪያው ውስጥ ያሉትን የውይይት ጥያቄዎች በመጠቀም ጥናቱን ይበልጥ ፍሪያማ ማድረግ ይቻላል፡፡ በጥያቄዎቹ ላይ አስተያየት ወይም ማሻሻያ ቢኖርዎ በሚከተለው የኢ-ሜይል አድራሻ ይጻፉልን፡፡ tsegaewnet@gmail.com መልካም የጥናት ጊዜ፡፡
Sign in to Google to save your progress. Learn more
Email *
1 ትንቢተ ዕንባቆም እግዚአብሔር በባቢሎናውያን አማካይነት በይሁዳ ላይ ስለሚያመጣው ቅጣት የሚተነብይ ቢሆንም፥ ዓላማው የእግዚአብሔርን ቅንና ትክክለኛ ፍርድ መመርመር ነው። *
1 point
2 ሰው ስለ እግዚአብሔር የአሠራር መንገዶች የመጠየቅ መብት የለውም። *
1 point
3 እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመቅጣት የተጠቀመበት ሰው ወይም መንግሥት መልካም ሰው እና መንግሥት መሆኑን ከዕንባቆም መጽሐፍ መረዳት እንችላለን፡፡። *
1 point
4 የይሁዳና የአሦር መንግሥታት እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ከመፍረዱ በፊት ለብዙ ዘመናት ቆይተዋል። ባቢሎናውያን ግን በእግዚአብሔር ሳይቀጡ የቆዩት ለ__________ ዓመታት ብቻ ነው። *
1 point
5 እግዚአብሔር ሰውን የሚያጸድቀው በሥራ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ባለው እምነት መሆኑን ለመገልጥ በአዲስ ኪዳን ሳይቀር በተደጋጋሚ ተጠቅሶ የምናገኘው የዕንባቆም ጥቅስ የቱ ነው? *
1 point
6 እግዚአብሔር ይሁዳን ለመቅጣት ባቢሎንን በተጠቀመ ጊዜ በይሁዳ መከራቸውን ያዩ በርካታ ጻድቃን ሰዎች ነበሩ፡፡ *
1 point
7 ዕንባቆም የሚያስተምረን እምነታችን በእግዚአብሔር እንጂ በዙሪያችን ባሉ ሁኔታዎች ላይ መመሥረት እንደሌለበት ነው። *
1 point
8 በእግዚአብሔር ካመንን ሁልጊዜ ባለጸጎች እንሆናለን ወይም ከበሽታችን እንፈወሳለን የሚለው ትምሕርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው ነው፡፡ *
1 point
9 ልንቆጣጠር የምንችለው ምርጫችንን እንጂ ምርጣችን የሚያስከትላቸውን ነገሮች ወይም ውጤቶች አይደለም። *
1 point
10 ዕንባቆም ለእግዚአብሔር ያቀረበው የመጀመሪያ ጥያቄ፣ "እግዚአብሔር በይሁዳ የሚገኘውን ክፋት ያልቀጣው ለምንድን ነው?" የሚለው ነው፡፡ *
1 point
11 ዕንባቆም እግዚአብሔርን የጠየቀው ሁለተኛ ጥያቄ፣ "ጻድቅና ትክክለኛ ፍርድ ሰጭ የሆነው እግዚአብሔር የይሁዳን ኃጢአት ከእርሷ ይበልጥ ኃጢአተኞች በሆኑት በባቢሎናውያን አማካይነት እንዴት ይቀጣል?" የሚል ነበር፡፡ *
1 point
12 እግዚአብሔር አንድን ሰው ተጠቀመበት ማለት ደገፈው ማለት አይደለም። *
1 point
13 በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከሚገኙ እጅግ ውብ መዝሙራት ወይም ጸሎቶች አንዱ ዕንባቆም 3 ነው። *
1 point
14 የእምነት ዋስትናው በእግዚአብሔር ላይ እንጂ ከእግዚአብሔር በሚሰጡ በረከቶች ላይ አይደለም፡፡ *
1 point
A copy of your responses will be emailed to the address you provided.
Submit
Clear form
reCAPTCHA
This content is neither created nor endorsed by Google. Report Abuse - Terms of Service - Privacy Policy