የቅኔ ተማሪዎች መመዝገቢያ ቅጽ
የቅኔ ትምህርትን ጉባኤ ቤት ተገኝተው መማር ለማይችሉ ሁሉ!

"ቅኔ የምስጢር ዋሻ፣ የአእምሮ ማደሻ፣የእውቀት ማጎልመሻ " እንዲሉ የአባቶቻችን የጥበብ እና ፍልስፍና በር የሆነውን  'ቅኔ' በቀን 2 ሰዓት በመስጠት ቦታ ሳይገድበን  ኑ አብረን እንማር፡፡

3ተኛ ዙር!

ስለ ትምህርቱ መግለጫ፡-


✅መቼ ተጀመረ?
መርሀ ግብሩ መስከረም 2015 የተጀመረ ሲሆን ባለፉት አምስት ወራት 45 ተማሪዎችን ከሁለት ከፍሎ የአበውን ጉባኤ መልክ በጠበቀ መልኩ እያስተማረ ይገኛል።

✅መምህሩ ማን ነው?
   መ/ር ላዕከ ማርያም ሳሙኤል ሲሆኑ የቅኔ መምህር እና የአፕለይድ ኬምስትሪ አስተማሪ ናቸው፡፡ አንድ መርሀ ግብር ከ20  ተማሪ በላይ ማስተናገድ ስለማይችል ለእያንዳድኑ 20 ተማሪ አዲስ መምህር ይመደብለታል።

✅ትምህርቱ ለማን ተዘጋጀ?
   ከጀማሪ እስከ ዘራፊ አጠቃላይ ቅኔን ለማወቅ እና ፈቃደኛ ለሆነ ማነኛውም ሰው፡፡

✅ትምህርቱ በምን ይሰጠል?

በተማሪዎቹ ምርጫ የተወሰነ ሲሆን እስካሁን እየተሰጠ ያለው በtelegram እና  በYouTube ነው:: ተማሪዎቹ እያተማሩ ያሉበት መንገድ በምስል፤ በቪድዮ፤ በጽሑፍ እና በድምጽ ነው።

✅መቼ ይሰጣል?

መደበኛ የተምህርት ቀናት(የወንበር ቀናት):- 3 ቀናት በሳምንት ሲሆን በቀን 2 ሰአት ነው፡፡ ቀኑ እና ሰአቱ የተወሰነው በተማሪዎች ምርጫ ነው፡፡
መደበኛ ያልሆኑ የትምህርት ቀናት ፡-በሚመረጠው የመማሪያ ሚድያ ላይ  መምህሩ በቀን 6 ሰዓት ሙሉ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተማሪዎች እርስበርሳቸው አብረው እንዲቀጽሉ ይመቻችላቸዋል፡፡

✅የትምህርት ይዘት ምን ይመስላል?
በዋናነት
1.የግስ አወራረድ
2.እርባ ቅምር እና የቅኔ ዘረፋ
3. ታሪክ እና  ቅኔ ነገራ 
4. የአእመረ እርባታ እና  የይቤ እርባታ 
5. ዜማ ልክ(ቢር ተገብሮ)

በተጨማሪ
 የውዳሴ ማርያም ትምህርት፣ የዳዊት፣ የወንጌላት እንዲሁም የተአምራት የንባብ ትምህርት በግል ይሰጣል።
 
ከላይ የተዘረዘሩት በመርሀ ግብር ምድባቸው እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡
የበለጠ ወደ ትምህርቱ ሲገቡ የጊዜ ሰሌዳውን የሚያውቁ ይሆናል፡፡

✅ሰርትፊኬት አለው?

ለጊዜው ትኩረታችን ማስተማር ላይ ስለሆነ ሰርትፊኬት አናዘጋጅም። ነገር ግን እንደ አባቶቻችን ስርዓት በመምህርዎት ብቁ ሆኖ ሲገኙ መምህሮት የሚያስቀኙ ይሆናሉ። ተቀኝተዋል የሚለውን ማዕረግ በመምህርዎት የሚሰጥ ይሆናል፡፡


⚠️ለመመዝገብ የሚከተሉትን ማሟላት ግድ ይለዎታል።

1/ለመማር የሚረዳ ስልክ/ኮምፒውተር(smart phone/Computer)
2/ቢያንስ ቢያንስ በሳምንት 3 ቀን በቀን 5 ሰአት ያልተቋረጠ ኢንተርኔት(ያልተገደበ የኢንተርነት አገልግሎት ቢሆን ይመረጣል)
3/በቀን ቢያንስ 2 ሰዓት መስጠት የሚችሉ መሆን አለበት
3/ወርሃዊ ክፍያ መክፈል መቻል
Sign in to Google to save your progress. Learn more
ሙሉ ስም? *
አሁን የሚኖሩበት ሀገር *
Next
Clear form
Never submit passwords through Google Forms.
This content is neither created nor endorsed by Google. Report Abuse - Terms of Service - Privacy Policy