የትንቢተ አሞጽ መግቢያ
ጥያቄዎቹን ከመስራትዎ በፊት ለጥናት አመቺ ጊዜ መድበው በጸሎት የጥናቱን ክፍል እና ከላይ የቀረበውን ማብራሪያ በጥንቃቄ እንዲያነቡ እንመክራለን፡፡ ጥናቱን የሚያደርጉት  በቡድን ከሆነ (Bible study group)፣ በማብራሪያው ውስጥ ያሉትን የውይይት ጥያቄዎች በመጠቀም ጥናቱን ይበልጥ ፍሪያማ ማድረግ ይቻላል፡፡ በጥያቄዎቹ ላይ አስተያየት ወይም ማሻሻያ ቢኖርዎ በሚከተለው የኢ-ሜይል አድራሻ ይጻፉልን፡፡ tsegaewnet@gmail.com መልካም የጥናት ጊዜ፡፡
Sign in to Google to save your progress. Learn more
Email *
1 ትንቢተ አሞጽ ስለ እውነተኛ፥ ንጹሕና በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ስላለው ሃይማኖት ይናገራል። *
1 point
2 መዘመር፥ መጸለይ፥ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ወይም መመስከር የመሳሰሉትን ተገቢ የሆኑ ሃይማኖታዊ ድርጊቶችን ብንፈጽምም እንኳ ድሆችን፣ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና የሙት ልጆችን ለመሳሰሉ እርዳታ ለሚያሻቸው ሰዎች የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማድረግ ካልጣርን እውነተኛውን ሃይማኖት እየተከተልን አለመሆናችንን ያሳያል፡፡ *
1 point
3 እግዚአብሔር ይበልጥ ደስ የሚሰኘው በሃይማኖታዊ አምልኮ (ለምሳሌ መሥዋዕቶችን በማቅረብ) ሳይሆን በፍርድ፥ በጽድቅ፥ በፍቅርና ለድሆች በሚደረግ ምሕረት ነው፡፡ *
1 point
4 የትንቢተ አሞጽ ጸሐፊ አይታወቅም፡፡ *
1 point
5 አብዛኛዎቹ ነቢያት የነቢይነትን አገልግሎት ያከናውኑ የነበረው ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው ሲሆን፥ አሞጽ ግን እንደዚያ አልነበረም። *
1 point
6 አሞጽ በሕዝቡ ላይ ካቀረባቸው ወቀሳዎች አብዛኛዎቹ ዛሬ በእኛ ላይ ሊቀርቡ የሚችሉ አይደሉም። *
1 point
7 አሞጽ ትንቢቱን የጻፈበትን ዘመን የሚቆጥረው ከዳዊትና ከሰሎሞን አገዛዝ በኋላ ከተነሡት ሁለት ታላላቅ የእስራኤል ንጉሥ (ዳግማዊ ኢዮርብዓም) እና የይሁዳ ንጉሥ (ዖዝያን) ዘመነ መንግሥት ጋር በማያያዝ ነው። *
1 point
8 አሞጽ ባገለገለበት ዘመን በእስራኤል ምድር የፖለቲካና የኢኮኖሚ መረጋጋት ቢኖርም እንኳ ሕዝቡ በመንፈሳዊ፥ በማኅበራዊና በሥነ-ምግባር ክፋት ተሞልተው ነበር። *
1 point
A copy of your responses will be emailed to the address you provided.
Submit
Clear form
reCAPTCHA
This content is neither created nor endorsed by Google. Report Abuse - Terms of Service - Privacy Policy